
ቅማንት የጠየቀው በቅማንትነቱ እውቅና አግኝቶ ራሱ በዴሞክራሳዊ ምርጫ በሚመርጣቸው ልጆቹ እንዲተዳደር እንጂ ሌላ ደባል ማንነት ፍለጋ አይደለም። ቅማንት የራሱ የሆነ ወጥ ባህል፣ ትውፊት፣ ስነልቡና፡ ታሪክ፡ ማህበራዊ ግንኙነት፡ ቋንቋ፡ ወዘተ ያሉት ህዝብ ነው። የቅማንት ህዝብ ትግልም ዓላማው ይህን የራሱ የሆኑ እሴቶቹን በማጎልበት እሱነቱን ለማሳደግ ነው። ቅማንት የተበደረው ሌላ ማንነት የለውም። ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ብሎም ከማንም ጋር አይጠጋም። መጠጋት ራስን በራስ የመለወጥን ብርታት ያጠፋል። እንደራስህ የምታስብበትንም ነጻነት ያ
ቅማንት የጠየቀው በቅማንትነቱ እውቅና አግኝቶ ራሱ በዴሞክራሳዊ ምርጫ በሚመርጣቸው ልጆቹ እንዲተዳደር እንጂ ሌላ ደባል ማንነት ፍለጋ አይደለም። ቅማንት የራሱ የሆነ ወጥ ባህል፣ ትውፊት፣ ስነልቡና፡ ታሪክ፡ ማህበራዊ ግንኙነት፡ ቋንቋ፡ ወዘተ ያሉት ህዝብ ነው። የቅማንት ህዝብ ትግልም ዓላማው ይህን የራሱ የሆኑ እሴቶቹን በማጎልበት እሱነቱን ለማሳደግ ነው። ቅማንት የተበደረው ሌላ ማንነት የለውም። ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ብሎም ከማንም ጋር አይጠጋም። መጠጋት ራስን በራስ የመለወጥን ብርታት ያጠፋል። እንደራስህ የምታስብበትንም ነጻነት ያሳጣሃል። ከሌላ ተጠግተህ የምታተርፈው ምንም ነገር የለም። ይልቁንም ያለህን ታጣለህ። ስለዚህ ቅማንት ሆይ! መብትህን በራስህ ታግለህ እንዳስከበርከው ሁሉ ቀሪውን ትግልህም እንጀግናው ልጅህ አጼ ቴወድሮስ በራስህ ውስጥ ያለህን መልካም ራእይ አደራጅተህ እውን ለማድረግ በራስህ ልጆች፡ በራስህ እቅድ፡ በራስህ ሃብት ተመስርተህ ታገል። ለዚህም ዓላማህ እውን መሆን በትግልህ ጸንሰህ የወለድከው ድርጅትህ #ቅዴፓ ከጎንህ ነው። አንዳንድ የፌስቡክ ሰራዊቶች የሚያራግቡት ያልሆኑ ጋብቻዎች የራሳቸው የግለሰቦች እንጂ ያንተ ወይም የእውነተኛዎች ታጋይ ልጆች አይደለም። እኛ ቅማንቶች የሌሎች ሕዝቦች (አማራ፡ አገው፡ ብሌን፡ ትግራይ፡ ወልቃይት፡ ፈላሻ) መሰረቶች እንጂ ከእነዚህ ከእንዳቸውም አልጠፈጠርንም። እናም አባትን ልጅ ልጅን አባት ለማድረግ የሚሞክሩ ግለሰቦች በዘላቂው የቅማንት ሕዝብ እጣ ፋንጣ ጥቁር ነጥብ ለመጣል የሚታገሉ ናቸው። ለቅማንት ሕዝብ ሁሉም ህዝቦች እኩል ቀረቤታ አላቸው እንጂ አንዱን አርቀን ሌላውን የምናቀርብበት ምንም አይነት ታሪካዊና ሳይንሳዊ መረጃ የለንም። የአማራ ሕዝብ ወንድማችን ነው። ሌሎችም እንዲሁ።
መላው የቅማንት ህዝብ እንኳን ደስ ያለን ቅዴፓ ተመሰረተልን።
"""""""""""""
በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲ መመዝገቢያ አዋጅ 573/2000 መሠረት ሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በአይከል ከተማ በተደረገው የመሥራች ...
የቅማንትን ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ህዝቡ ተከታታይነት ያለው የተቃውሞ ሰላማዊ ትግል በማካሄድ ላይ ነው።
ዛሬም እንደከዚህ ቀደሙ መስከረም 04/2011ዓ/ም የአይከል ከተማና አካባቢ የቅማንት ብሄር ተዎላጆችና ደጋፊዎች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። የሰልፋ ዋና አላማም ፡ የቅማንት ህዝብ የጠየቀው ጥያቄ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ በግፍ የታሰሩየቅማንት ኮሚቴዎች ይፈቱና የቅማንት ህዝብን የማይዎክሉ አመራሮች መስከረም ሶስት 2011 ዓ/ም ህዝብን ለማጫረስ በመምጣታቸውና የእነሱን እኩይ ተግባር
የቅማንትን ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ህዝቡ ተከታታይነት ያለው የተቃውሞ ሰላማዊ ትግል በማካሄድ ላይ ነው።
ዛሬም እንደከዚህ ቀደሙ መስከረም 04/2011ዓ/ም የአይከል ከተማና አካባቢ የቅማንት ብሄር ተዎላጆችና ደጋፊዎች ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። የሰልፋ ዋና አላማም ፡ የቅማንት ህዝብ የጠየቀው ጥያቄ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ በግፍ የታሰሩየቅማንት ኮሚቴዎች ይፈቱና የቅማንት ህዝብን የማይዎክሉ አመራሮች መስከረም ሶስት 2011 ዓ/ም ህዝብን ለማጫረስ በመምጣታቸውና የእነሱን እኩይ ተግባር ለማውገዝ ያለመ እንደነበርም የሰልፋ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቅማንት ኮሜቴ አባል መምህር መካሻው አበው ተናግረዋል። በመጨረሻም የቅማንት ህዝብ በነውጠኛ አመራሮች መመራት እንደሌለበትና የተጠየቀውን ጥያቄ ለመድፈቅ የሚቀሳቀሱ አመራሮች ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና በቤተሰብ ምክር እንዲሰጥ ሰልፈኞ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ፍትህ ለቅማንት ህዝብ!!!!!
ቅማንት የጠየቀው በቅማንትነቱ እውቅና አግኝቶ ራሱ በዴሞክራሳዊ ምርጫ በሚመርጣቸው ልጆቹ እንዲተዳደር እንጂ ሌላ ደባል ማንነት ፍለጋ አይደለም።
Sign up to receive updates from KDP
Copyright © 2018 KDP
United Kemant for common good!